እግዚአብሔርን እንዴት በግል ማወቅ እንደምትችል ለመረዳት
እግዚአብሔርን እንዴት ማወቅ እንደሚቻል ትምህርተ ሥላሴን መረዳት
ከጭፍን እምነት ባሻገር
ውሸታም ፣ ወንበዴ ወይስ ጌታ?
በመንፈስ ቅዱስ መሞላት እና መመራት
ፀሎትን የምንረዳበት መንገድ ስለእግዚአብሄር ያለንን እይታ ይቃኛል
መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት አስበው ነገር ግን ከየት መጀመር እንዳለብዎ አያውቁም ይሆን?
የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞችን ያጥኑ ፣ እንዴት እንደ ተፃፈ ይረዱ
ደቀመዝሙርነት ምንድነው?
ሌሎች እንዲያድጉ እርዳቸው
ሌሎች እንዲያድጉ እርዳቸው
ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ ደቀመዛሙርቶችን ማፍራት
ሌሎች እንዲያድጉ እርዳቸው
ውጤታማ ስልጠና ለተሻለ ነገ
ለሚያድግ እንቅስቃሴ በተሳካ ሁኔታ ያቅዱ
የተማሪ-መር እንቅስቃሴ
የመሪ -መር አገልግሎት
Today, the Lord is using the internet to reach millions of people to begin a living relationship with him.
ናሽናል ኦፔሬሽን
አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ
የጸሎት እንቅስቃሴ
የሰው ሀብት እና የአመራር ዕድገት
ልዩ ልዩ አገልግሎቶች
እንዴት ከክርስቶስ ጋር ወደአለ ወዳጅነት ከ እያንዳንዱ ሰው ጋር መጓዝ እንደምንፈልግ
ስለ ወንጌል እና አለምን ስለምናገለግልበት ጥሪያችን
ዶ/ር ታሪኩ ያደገው በኢትዮጵያ በጊ በሚባል አካባቢ ሲሆን ወላጆቹ በፍቺ የተለያዩት ገና የ1 ዓመት ህፃን እያለ ነበር::
የተለምዶ የሆነውንና እናትህ ከተወችህ ማንም ሊወድህ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ ይዞ አደገ::
ዶ/ር ታሪኩ ወንድሙ ስለ ኢየሱስ እስከነገረው ጊዜ ድረስ ህይወቱ የህመም፣ የብቸኝነትና የተስፋ መቁረጥ ነበር:: ከዚያ ቀን በፊት “ፍቅር የሚባለውን ቃል” ሰምቶ አያውቅም ነበር::
በ13 ዓመቱ ዶ/ር ታሪኩ እምነቱን በክርስቶስ ላይ በማድረግ ለሌሎች ሁሉ ስለጌታ ለመናገር ተነሳሳ:: ከዚያች ቀን ጀምሮ የሚባዛ ደቀመዝሙር ለመሆን ፍላጎት አደረበት፤ ይህንንም 25 ለሚጠጉ አመታት ሲያከናውን ቆይቷል::
አሁን ከክሩ (Cru) ጋር አብሮ እየሰራ በዙምባቡዌ ውስጥ እየኖረ ይገኛል:: በ24 የአፍሪካ ሀገራት የሚባዙ ደቀመዛሙርትን በማነሳሳት ላይ ይገኛል::
ዶ/ር ታሪኩ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ስድስት መርሆች ማንኛውም ሰው ክርስቶስን ያማከለ የሚባዛ ደቀመዝሙር እንዲሆን ይረዱታል ብሎ ያምናል:: ይህም ከልብ የመነጨ ፍላጎቱ ለሰዎች ካለው ፍቅርና ሰዎችን እስከመጨረሻው ለመርዳት ካለው ፍላጎት የመነጨ ነው::
ዶ/ር ታሪኩ ቦስኮ የሚባል በሩዋንዳ የሚኖር የመጀመሪያ ዓመት የኮሌጅ ተማሪን ያስታውሳል:: ቦስኮ “ሩዋንዳን በወንጌል የመገለባበጥ” ፅኑ ፍላጎት ነበረው:: የተማሪዎች መሪ ሳለ በ4 ዓመታት ብቻ የክርስቲያን ተማሪዎች ማዕከል ከ1 ወደ 38 (ከ1 ዩኒቨርሲቲ ወደ 14 ዩኒቨርሲቲ) እንዲያድጉ ረድቷል:: ይህ ሊሆን ከቻለባቸው ምክንያቶች አንዱ ለ40 ቀናት በጥቅምትና በህዳር ወራት በሩዋንዳ የፆምና ፀሎት ጊዜ በመኖሩ ነው:: የተለያዩ ሀገራትንና ካምፓሶችን በወንጌል ለመድረስ ዶ/ር ታሪኩ ከ7 እስከ 40 ቀናት ድረስ ፆምና ፀሎት እንዲደረግ ይመክራል::
ፀሎት አክብሮት መስጠት፣ ምስጋና፣ ንስሀ፣ ምልጃና ልመናን ያጠቃልላል:: ዶ/ር ታሪኩ “ፀሎት የህይወት ዘይቤ ነው” ይላል:: ስትቀመጥም ሆነ ስትነሳ እንደሚያስፈልግህ እንደ እስትንፋስህ ነው::
“መንፈስ ቅዱስ በአንተ ውስጥ ሲኖር ወደ ራስህ አትመለከትም” ይላል ዶ/ር ታሪኩ:: ባለፈው ዓመት በዛምቢያ ብቻ ራሔል የተባለችው የዛምቤያው ክሩ ቅርንጫፍ አገልግሎት ባልደረባ (ዶ/ር ታሪኩ የሚከታተላት) ያሰለጠነቻቸው ተማሪዎች አራተኛ መንፈሳዊ የደቀመዝሙር ትውልድ ላይ ደርሰዋል:: በአሁኑ ወቅት ደግሞ 75 የሚሆኑ ደቀመዛሙርት ወደ 225 ለማደግ በመሰልጠን ላይ ይገኛሉ::
“አገልግሎቴ በተማሪዎች የሚመራ ነው” የሚለው ዶ/ር ታሪኩ “የሹፌሩ መቀመጫ ላይ ከዚህ በኋላ የለሁም” ይላል፡፡
ዶ/ር ታሪኩ በኢትዮጵያ ከሚኖር ምስጋናው ከተባለ ተማሪ ጋር ተገናኝቶ ቡና እየጠጡ ተጨዋወቱ፡፡ ምስጋናው ከገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ከተማ በመምጣቱ ዓይናፋርና የሚፈራ ሰው ነበር:: የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቁንቋን መናገር ባይችልም መሠረታዊ የንግድ ቋንቋን ይችል ነበር:: ምስጋናው ክርስቲያን ሲሆን ዶ/ር ታሪኩም ለወንጌል ያለውንም ጥልቅ ፍቅር ተመለከተ፡፡ ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ጥናት ጋብዞት በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጲያ በተዘጋጁ መከታተያ የትምህርት መረጃዎች ደቀመዝሙርነትን አስተማረው፡፡
ለምስጋናው እየፀለየና እያበረታታው በክርስቶስ ያለውን ማንነቱን እንዲያውቅም ረዳው፡- “ልታደርገው ትችላለህ:: አንተ የክርስርስቶስ አምባሳደር ነህ” እያለ ይነግረው ነበር፡፡
ከአራት ወራት በኋላ ምስጋናው በመውጣት እምነቱን ማካፈል ጀመረ:: ሦስት ተማሪዎችም ክርስቶስን ተቀበሉ:: እያስተማረና ደቀመዝሙርነትን እያሰለጠናቸው በ6 ወር ውስጥ ቡድኑ ወደ 10፣ ከአንድ አመት በኋላም ወደ 120 ሰዎች አደገ፡፡
ጆን የተባለው ተማሪ መሪነትን እንዲቀበል ሲጠየቅ እንደሚችል እርግጠኛ አልነበረም:: ብቁ እንደሆነ ሊያምን አልቻለም ነበር :: አንድ ቀን ለብዙ ሰዓት ያህል ወንጌልን ለሌሎች ለመናገር ወጣ:: ካናገራቸው ሰዎች መሃል አራቱ እምነታቸውን በክርስቶስ ላይ ለማድረግ ፍላጎት አሳዩ:: ነገር ግን ከእነርሱ ጋር ከመፀለይ ይልቅ ዶ/ር ታሪኩ መጥቶ እንዲፀልይላቸው ጠየቀው:: ዶ/ር ታሪኩም ጆንን ላለማሳፈር ጥያቄውን ተቀብሎ ፀለየላቸው:: ከዚያ በኃላ ግን ዶ/ር ታሪኩ ጆንን ለብቻው በማናገር ለፀሎት እርሱ መጥራት እንደማያስፈልገው ነገረው:: በሚቀጥለው ጊዜ ጆን 17 ሰዎችን ወደ ጌታ ሲመራ ለእያንዳንዳቸው ራሱ እየፀለየ ነበር::
ዶ/ር ታሪኩ ደቀመዛሙርት በመጀመሪያ ጊዜ ነገሮችን በትክክል ላይሰሩ እንደሚችሉ ያውቃል:: “አንተ ማስተማር እንደምትችለው ማስተማር ባይችሉም ከአንተ ግን መማር ይችላሉ:: በመሳሳት ሊወድቁ እንደሚችሉ እያሰብክ መሳሳት እንዲችሉ ነፃነትን ስጣቸው” ይላል::
አንተ የወንጌልን መልዕክት ለደቀመዛሙርት የምታስተምር መልዕክተኛ ነህ:: ባህሪህ የመልዕክትህን ያህል አንዳንዴም ደግሞ በበለጠ ለሰዎች ምስክር ሊሆን ይችላል ይላል ዶ/ር ታሪኩ:: ታማኝ ነህ? በጌታ ያለህ የግል ህይወትህ እንዴት ነው?
በተጨማሪም መልዕክትህን አስብ:: ቀላልና ግልጽ ነው? በልዩ ልዩ ባህሎች ውስጥ መሰማት የሚችል ነው?
መልዕክትህን እንዴት ትናገራለህ? ዘዴዎችህስ ምንድናቸው? ዶ/ር ታሪኩ ዘዴው እንደ እግር ኳስ ቀላል ነው ይላል:: በሁሉም ቦታ ታዋቂና እንደሆነው እንደ ስፖርቱ መሰረታዊ መርሆ የማይከብድና ዝም ብሎ ኳሱን የመምታት ያህል ነው:: የወንጌል መልዕክትህን ወደዚያ ዓይነት ዕይታ ማምጣት ትችላለህ?
ለዶ/ር ታሪኩ የሚባዙ ደቀመዛሙርትን መፍጠር ማለት ተስፋ ለሌላቸው ተስፋ መስጠት ነው::
“ተስፋ ያጡ ሰዎች ጌታን ሲያገኙ ተስፋን ያገኛሉ:: ለእኔ ወንጌልን መስበክና ደቀመዛሙርን ማፍራት እጅ ለእጅ የሚሄዱ ነገሮች ናቸው:: ዓለምን በራስህ ብቻ መድረስ አትችልም” ይላል፡፡
©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።