እግዚአብሔርን እንዴት በግል ማወቅ እንደምትችል ለመረዳት
እግዚአብሔርን እንዴት ማወቅ እንደሚቻል ትምህርተ ሥላሴን መረዳት
ከጭፍን እምነት ባሻገር
ውሸታም ፣ ወንበዴ ወይስ ጌታ?
በመንፈስ ቅዱስ መሞላት እና መመራት
ፀሎትን የምንረዳበት መንገድ ስለእግዚአብሄር ያለንን እይታ ይቃኛል
መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት አስበው ነገር ግን ከየት መጀመር እንዳለብዎ አያውቁም ይሆን?
የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞችን ያጥኑ ፣ እንዴት እንደ ተፃፈ ይረዱ
ደቀመዝሙርነት ምንድነው?
ሌሎች እንዲያድጉ እርዳቸው
ሌሎች እንዲያድጉ እርዳቸው
ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ ደቀመዛሙርቶችን ማፍራት
ሌሎች እንዲያድጉ እርዳቸው
ውጤታማ ስልጠና ለተሻለ ነገ
ለሚያድግ እንቅስቃሴ በተሳካ ሁኔታ ያቅዱ
የተማሪ-መር እንቅስቃሴ
የመሪ -መር አገልግሎት
Today, the Lord is using the internet to reach millions of people to begin a living relationship with him.
ናሽናል ኦፔሬሽን
አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ
የጸሎት እንቅስቃሴ
የሰው ሀብት እና የአመራር ዕድገት
ልዩ ልዩ አገልግሎቶች
እንዴት ከክርስቶስ ጋር ወደአለ ወዳጅነት ከ እያንዳንዱ ሰው ጋር መጓዝ እንደምንፈልግ
ስለ ወንጌል እና አለምን ስለምናገለግልበት ጥሪያችን
የሚከተሉት መርሆዎች በግል ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነትን እንዴት በክርስቶስ በኩል መጀመር እንደሚችሉ ያብራራሉ።
"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡”(ዮሐ 3፡16)" 1
ክርስቶስ እንዲህ አለ፡- ““እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ፡፡”(ዮሐ 10፡10)” 2
“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፡፡(ሮሜ 3፡23” 3
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ከእርሱ ጋር የቀረበ ግንኙነት በመመስረት በደስታ እንዲኖር ነበር፡፡ነገር ግን ሰው በራሱ መንገድ ለመጓዝ በመምረጡ ግንኙነታቸው ተቋረጠ፡፡ በራሳችን መንገድ ስንጓዝ ለእግዚአብሔር የማንታዘዝና ለርሱም ግድ የሌለን እንሆናለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አይነቱን አስተሳሰብ ነው ኃጢአት ብሎ የሚጠራው፡፡
“እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፡፡”(ኢሳ 53፡6)
“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና” (ሮሜ 6፡23) ይህም ሞት በመንፈስ ከእግዚአብሔር መለየት ማለት ነው፡፡ 4
ይህ ስዕል የሚያሳው እግዚአብሔር ቅዱስ ሰው ደግሞ ኃጢአተኛ በመሆኑ በመካከላቸው ትልቅ መለያየት መኖሩን ነው፡፡ ቀስቶቹ የሚያመለክቱት ሰው በራሱ መንገድ ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ እንዴት እንደሚጥር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የሃይማኖት ስርአቶችን በመፈፀም፣ ቤተክርስትያን ሳያቋርጥ በመመላለስ፣ መልካምን ስራ በመስራት፣ ሰውን ባለመጉዳት፣ወ.ዘ.ተ. ነገር ግን ሰውን ጥረቱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበው አልቻለም፡፡
“ነገር ግን ገና ኃጢያተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል፡፡ (ሮሜ. 5፡8)” 5
“…ክርስቶስ ስለ ኃጢያታችን ሞተ ተቀበረም መጽሐፍ እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፣ …” 6
“ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- 'እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ' (ዩሐ› 14፡6)” 7
ይህ ስዕል የሚያሳየው እኛን ወደ ራሱ ሊመልሰን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ይህንንም ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በመስቀል ላይ ስለእኛ እንዲሞት በመላክ ፈጽሞታል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሁላችንም በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር መድረስ እንችላለን፡፡
“ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው(ዩሐ.1፡12)” 8
“ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም(ኤፌ. 2፡8-9)፡፡” 9
በግላችን ክርስቶስን ወደ ሕይወታችን በመጋበዝ ልንቀበለው ይገባል
“እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል (ራዕ. 3፡20)” 10
ክርስቶስን መቀበል የሚከተሉትን ያጠቃልላል
- ኃጢያተኛ መሆናችንን ማወቅና ከኃጢያታችን ለመመለስ በመወሰን ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት
- ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢያታችንን ይቅር እንደሚልና ወደ ሕይወታችንም እንደሚመጣ ማመን
- ክርስቶስ በእኛ ውስጥ እንዲኖር መፍቀድና እርሱን ማሳየት
ይህ ሰው የራሱን ሕይወት የሚቆጣጠረው ራሱ ነው፡፡ ክርስቶስ እስከ አሁንም ድረስ ከሕይወቱ ውጪ ነው ሕይወቱን በተለያየ አቅጣጫ የሚመራው ራሱ ነው ውጤቱም ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ማጣት ነው፡፡ የዚህ ሰው ሕይወት ተቆጣጣሪ ክርስቶስ ነው፡፡ በማንኛውም አቅጣጫ ክርስቶስ ሕይወቱን እንዲቆጣጠርለት ፈቅዷል ውጤቱም ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም መፍጠር ነው፡፡እነዚህ ሁለት ክቦች ሁለት አይነት ሕይወት ይወክላሉ፡-
በእኔነት ቁጥጥር ስር ያለ ሕይወት
በክርስቶስ ቁጥጥር ያለ ሕይወት
ከርስቶስን እንደግል አዳኝህና ጌታህ አድርገህ መቀበል የምትችለው በፀሎት ወደ ሕይወትህ እንዲመጣ በመጋበዝና በቃሉ እንደተናገረው እንደሚያደርግ በእርሱ በመታመን ነው፡፡ እግዚአብሔር ልብህን ስለሚያውቅ ልታታልለው አትችልም፡፡ ስለዚህ ፀሎትህ ከልብ የመነጨ መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ልትፀልይ ትችላለህ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ አንተን በግሌ ለማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ ስለ ኃጢያቴ በመስቀል ላይ ስለሞትክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አሁን ልቤን ከፍቼ አዳኜና ጌታዬ አድርጌ እቀበልሃለሁ፡፡ ኃጢያቴን ሁሉ ይቅር ስላልከኝና የዘላለም ሕይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ፤፤ በሕይወቴ ዙፋን ላይ ሆነህ ግዛኝ አንተ የምትፈልገው ዓይነት ሰው አድርገኝ፡፡ አሜን!አሁኑኑ ክርስቶስን በእምነት ልትቀበል ትችላለህ
©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።