በዲጂታል ስትራቴጂ አገልጋዮች

ሂሩት ጫካ

ዲጂታል ስትራቴጂስት

ሂሩት ጫካ ገለቱ እ/ኤ/አ በ2008 የእግዚሀብሄርን ጥሪ በመቀበል በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ/ በካምፓስ ክሩሴድ ፎር ክራይስት ኢንተርናሽናል አገልግሎቷን ጀመረች፡፡ 

የመጀመሪያ ዲግሪዋን በ2004 ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ ተቀብላለች፤ በመቀጠልም በክርስቲያን ካውንስሊንግ ማስተርስ ዲግሪዋን ከቪዝን ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ ተቀብላለች፤ በተጨማሪም ልጆችን በወንጌል የመድረስ ጥሪዋን የበለጠ ለማሳለጥ እንዲረዳት በሆሊስቲክ ቻይልድ ዴቨሎፕመንት ሁለተኛ ማስተርስ ዲግሪዋን እ/ኤ/አ ብ2015 አግኘታለች፡፡

በግሬት ኮሚሺን ሚኒስትሪ ውስጥ በተለያዩ የአገልግሎት መስኮች ላይ ላለፉት 12 አመታት አገልግላለች፡፡ በመጀመሪያ ለአገልግሎት የተሰማራችው ምዕራብ ኢትዮጵያ ነቀምቴ በሚባል ከተማ ውስጥ አዲስ የተከፈተውን የግሬት ኮሚሽን ቢሮ ከባለቤቷ ጋር ለማስተባበር ሲሆን የሴቶችን አገልግሎት ከማስተባበር በተጨማሪ የአስተዳደርና ፋይናንስ ኦፊሰርነትን ስራ በመስራት ለ 2 አመት አገልግላለች፡፡ በመቀጠልም ወደ ብሄራዊ ቢሮ የፋይናንስ ማናጀርነትን ስራ ለመስራት ተዘዋውራለች፤ ወደ ዲጂታል ስትራቴጂ የአገልግሎት ክፍል ከመቀላቀሏ በፊት ያገለገለችው በተማሪዎች መር አገልግሎት ውስጥ ነው፤ በአሁኑ ሰአት በዲጂታል ስትራቴጅ ንዑስ ክፍል ነጻ ሂወት አገልግሎትን በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡

ሂሩት ጫካ የእግዚሀብሄርን መንግስት ከባለቤቷ ጋር በመሆን እያገለገለች የምትገኝ ስትሆን፤ 3 ከማህጸንና 2 ከልብ ከወለደቻቸው ልጆች ጋር አብራ ትኖራለች፡፡


ስለ ሂሩት የበለጠ ለማወቅ እባክዎትን የሚቀጥለውን ሊንክ ይጫኑ፡ https://www.facebook.com/Hirutchaka/

ሂሩትን ይደግፉ

©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።