መሪዎችን ማብቃት

ውጤታማ የሆነ የቡድን መሪ መሆን

ህይወትን የሚለውጥ ደቀ መዝሙርነት ካበረታታን በኋላ የሚባዙ መሪዎችን ደግሞ ማፍራት አለብን።

ዓለምን ለመለወጥ እንዲቻል ከራሳቸው አልፈው የሚያስቡ፣ የነገ ዕይታ ያላቸውና ሌሎች ወደ መሪነት እስኪመጡ ድረስ የሚተጉ ሰዎች ማፍራት አለብን። 

ያሉበትን ዓለም ለመለወጥ እንዲችሉ መሪዎች ተከታዮችን ከማፍራት ብቻ ያለፈ ፍላጎት ሊኖራቸው ያስፈልጋል። መሪዎችን ማፍራት አለባቸው። ራሳቸውን ማባዛት አለባቸው። ያ ሲሆን ጠቅላላው የክርስቶስ አካል ይጠቀማል፡፡

እነዚህም መሪዎች በተማሩት ትምህርት መሰረት ባሉበት ካምፓስ፣ ማህበረሰብና ሀገር ዘላለማዊ ተፅዕኖ የሚያመጡ መሪዎች ይሆናሉ። በየቀኑ በቢዝነስና በመንግስት የአመራር ስፍራ ያሉ መሪዎች በመላው ማህበረሰብ ውስጥ በጉልህ የሚታዩ ተፅዕኖ አምጪ ውሳኔዎችን ያስተላልፋሉ። እነዚህ ውሳኔዎች ኢየሱስን ከልባቸው በሚከተሉ ወንዶችና ሴቶች የሚተላለፉ ቢሆን ዓለማችን እንዴት የተለየች ትሆን ነበር።

በክሩ (Cru) የዓዋቂ ባለሙያዎች አገልግሎቶች (ማለትም ክርስቲያን ኤምባሲ፣ የስራ አስፈፃሚዎች አገልግሎት፣ የህይወት ውስጣዊ ከተማ፣ የህይወት ገንቢዎች፣ የጦር ሃይሎች አገልግሎት እና ቅድሚያ ተባባሪዎች በተባሉ አገልግሎቶች) አማካኝነት ጠፍተው ያሉ ወንዶችና ሴቶችን ክርስቶስን ያማከሉ መሪዎች አድርጎ እንዲቀይራቸው እግዚአብሔርን እየለመንን ነው፡፡

በዓለም ዙሪያ ሁሉ መሪዎችን ለማሰልጠን እግዚአብሔር ክሩን እየተጠቀመ ነው።

ሳዲ ቫን ሩለር በኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ውስጥ ከክሩ ጋር በማገልገል የቆየችባቸው 6 ዓመታት በፍሪበርግ ጆርመን እርሷና ባለቤቷ ሌሎችን ማሰልጠን የሚችሉ ወጣት መሪዎችን በማብቃት ለሚኖራት ቆይታ አዘጋጅተዋታል፡፡ 

በ11 ወራት ውስጥ በፍሪበርግ ላይ  ቀጣይ የመሪዎች ትውልድን የሚያስነሱ 4 ሴቶችን ተዋወቀች፡፡ የመጀመሪያዋ እንደ ሳዲ ወደ ክሩ አገልግሎት የሚቀላቀሉ አዳዲስ ሰዎችን ለማሰልጠን የተዘጋጀች ነበረች። ሌላኛዋ በጀርመን ውስጥ ሌሎችን ለመድረስ እንዲረዳት በማማከር ዙሪያ ሁለተኛ ዲግሪዋን እየተማረች ነው። ሦስተኛዋ ለሁለተኛ ዓመት በድጋሚ ለማገልገል ከተማሪዎች ጋር መሆንን መረጠች። አራተኛዋ ደግሞ ወደፊት በሙሉ ጊዜዋ ወደ ፍሪበርግ ተመልሳ የማገልገልን ዕቅድ ይዛ የክሩ አገልግሎት አካል ሆናለች፡፡ 

ሳዲ፦ " እነዚህ ሴቶች ወንጌልን ሲኖሩት ማየትና ሌሎች ወንጌልን እንዲኖሩ ሲመሯቸው ማየት ያነቃቃኛል" ትላለች።

ኤሚሊዮ ካሪኡኪ ስለ ኢየሱስ እንዴት ለሌሎች መናገር እንዳለበትና የነገራቸውም ሰዎች እንዲሁ ስለ ኢየሱስ መናገር እንዲችሉ እንዴት ሊያነሳሳቸው እንደሚችል የተረዳው በኪያምቡ ኬንያ ዲስትሪክት የምትገኝ የአነስተኛ መፅሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ርዕሰ መምህር ሆኖ እያለ ነው። ይህንንም የተማረው የክሩ አገልግሎት አካል በሆነው የናይሮቢ ዓለም አቀፍ የስነ መለኮት ትምህርት ቤት (ኒስት) ሲሆን ኤሚሊዮም ወደያውኑ በራሱ መፅሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የሚገኙ 7 ሰዎችን ይህንን ሞዴል እንዲከተሉ ቀሰቀሳቸው ።

ባገኘውም ውጤት ተገረመ፡፡

ከኤሚሊዮ ተማሪዎች አንዱ በአካባቢው ወዳለ ወንዶች ልጆች የሚኖሩበት ቤት በመሄድ 10 ወጣት ወንዶች ክርስቶስን እንዲቀበሉ ረዳቸው። ከዚህያም እነዚህ አስሩ ወጣቶችን እንዴት ስለ ኢየሱስ መናገር እንደሚችሉ አሰለጠናቸው፡፡ በዚያም ቀን አብረዋቸው ከተሰበሰቡ ሌሎች 12 ልጆች መሃል 11ዱ ክርስቶስን ተቀበሉ

በኤሚሊዮ የመጀመሪያው ቡድን ውስጥ የነበሩት ሰባቱም ተማሪዎች አዲስ አማኞችን የሚከታተሉበት የየራሳቸውን ቡድን የመሰረቱ ሲሆን፤ አንዱም ተማሪ ከመዲናዋ ናይሮቢ ወጣ ባሉ ስፍራዎች ቤተክርስቲያንን በመትከል ላይ ይገኛል። ኤሚሊዮ ሌሎችን ወደ መምራት የሚያድግ ደቀ መዝሙርነት ምን እንደሆነ ተረድቷል። በክሩ የሚገኙ አገልጋዮችም ይህንን ዘዴ በእርሱ ትምህርት ቤት መጥተው እንዲያስተምሩ እየጋበዛቸው ይገኛል። 

የሚባዛ መሪነት ማለት ይሄ ነው፡፡

©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።