ዲጂታል ሚሽን

እንደ ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ የዲጂታል እስትራቴጂ ቲም ወንጌልን የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንድናገለግል የሚያደርጉን ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉን።እነዚህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ የተልኮ ስፍራችን እንዲሁም የውጊያ ቀጠናቸን መሆኑ ነው። ታላቁን ተልዐኮ ገቡን እንዲመታ እንደሚጥር አንድ ሚኒስትሪ ወደ ዓለም ሁሉ መሄድ እና ደቀመዛሙርትን ማፍራት ከጌታ የተቀበልነው ዋና ዓደራ ነው። ይህን ዓደራ ለመወጣት ደግሞ ዓለም ወዳለበት ስፍራ መሄድ ይኖርብናል።የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያሳዩን ደግሞ የአለማችን 60 በመቶ ህዝብ ከኢንተርኔት ጋር ተያይⶋ ይገኛል ቀሪው ህዝብ ደግሞ በቅርቡ ወደዚህ በይነ መርብ እንደሚቀላቀል ይግመታል።ክዚህ ለመርዳት እንደምንችለው የአለም ወደ አንድ መንደርነት እየተቀራረበች መሆኑ ነው ታዲይ ይህ ወንጌልን ወደ ዓለም ዳርቻ ይዞ ለመቅረብ ትልቅ እድል አይደለምን?

እዚህ በዲጂታል ሚሽን ቲም ውስጥ ሁለት ዋና ዋና የቤት ሰራዎች አሉብን።የመጀመሪያው የዲጂታል ሚሽን እንቅስቃሴን መገንባት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የዲጂታል ሚሽን አገልግሎትን መተግበር ነው። 

ከዚህ በታች የተዘርዘሩት ተግባራት በ ቡድኑ አባላት እና በ ተባባሪዎቻችው የሚተገበሩ ናቸው።

የዲጂታል እስትራቴጂን መንፈሳዊ እንቅስቃሴን ከመገንባት አንጻር

  1. የዲጂታል እስትራቴጂን ራእይ ለ አብያተክርስቲያናት፤ለሃይስኩል እና ካምፓስ የተማሪ ህብረቶች ማስተዋወቅ

  2. አብያተክርስቲያናት፤ለሃይስኩል እና ካምፓስ የተማሪ ህብረቶች የዲጂታል እስትራቴጂ ቡድን እንዲመሰርቱ እና የዲጂታል አገልግሎት እንዲጅምሩ ማገዝ

  3. አብያተክርስቲያናት፤ለሃይስኩል እና ካምፓስ የተማሪ ህብረቶች በተላያዩ የዲጂታል መሳሪያዎች እና ስልቶች ማስታጠቅ

  4. በመላው አገሪቱ የዲጂታል ሚሽነሪ አገልጋዮችን ማፍራት

  5. የዲጂታል ሚሽን አገልግሎት የጀምሩ  አብያተክርስቲያናት፤ለሃይስኩል እና ካምፓስ የተማሪ ህብረቶች መከታተል

  6. የኢንዲጂተስ ኮሚዩኒቲ ሁነቶችን ማዘጋጀት

የዲጂታል እስትራቴጂን አገልግሎት ከመተግበር አንጻር

  1. የተለያዩ ፕላት ፎርሞችን በመጠቀም ወንጌልን መስራት

  2. የማህበራዊ ሚዲያን አገልግሎትን ማስተዳደር

  3. የ ሞባይል መተግበሪያዎችነ ማስተዳደር

  4. የ ድህረ ገጾችን ማስተዳደር

  5. የ ዲጂታል ይዘቶችን ማዘጋጀት

የአገልሎታቸን የትኩረት ቦታዎች

  1. አብያተክርስቲያናት

  2. የሃይስኩል የተማሪ ህብረቶች

  3. የካምፓስ የተማሪ ህብረቶች

  4. የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች

  5. የመጽሃፍ ቅዱስ ኮሌጆች

የቡድኑ አባላት

  1. ሰናይ ቁምላቸው

  2. ቶኩማ ይገዙ

  3. ሙሉቀን መንግስቱ

  4. ረድኤት ክፈተው

©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።