አሶሺየትስ(ተባባሪዎች)
246
የመረጃ እና የቴክኖሎጂ ዘመን ተብሎ በሚጠራው በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር የወንጌልን አደራ ለሰው ልጆች ሁሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በፍጥነት እና በቀላሉ ለማድረስ ይቻለን ዘንድ የሚረዱ ብዙ እድሎችን እንደሰጠን እናምናለን።ቀደምት ክርስቲያኖች የሮም ነገስታት ለወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞቻቸው ሲሉ የሰሯቸውን መንገዶች ተጠቅመው ወንጌልን ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም ብሎም ወደ አህዛብ ሁሉ ማድረስ እንደቻሉ ሁሉ እኛም ኢንተርኔትን እና ሌሎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ እመርታዎችን በመጠቀም ወንጌልን ለሰዎች ሁሉ ለማድረስ እየተጋን እንገኛለን።
ይህንንም እንድናደርግ የሚያስገድዱን ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉን
የመጀመሪያው ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ የሚለው የተልእኮችን መርህ ነው።በአሁኑ ጊዜ ከአለማችን ህዝብ 2/3ተኛው መገኛውን ኢንተርኔት ላይ አድርጎአል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገሮችም ቢሆን ከእለት እለት በማይታመን ፍጥነት ብዙዎች ወደዚህ ቴክኖሎጂ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። ጎግልን በመሳሰሉ የመረጃ አሳሾች ደግሞ በየዕለቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ እግዚአብሄር፤ ስለ መንፈሳዊ ህይወት፤ ስለ ደስተኛነት እና ስለፍቅር የተመለከቱ የተለያዩ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ ታዲያስ ለነዚህ ሁሉ የህይወት ጥያቄዎች ምላሽ የሆነውን የወንጌል እውነትን እኛ ካላቀረብንላቸው ማን ያቀርብላቸዋል ? ደግሞስ ወደ አለም ሁሉ ልንሄድባቸው ከሚገቡን መንገዶች አንዱ ኢንተርኔት ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆ ን ይችላል?
ሁለተኛው ደግሞ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለዘመናችን ያመጣቸው መልካም እድሎች እንዳሉ ሁሉ የክፋት አሰራርም በቀላሉ በሰዎች መሀከል በፍጥነት እንዲሰራጭ መንገድ መክፈቱ ነው። ከነዚህም መሀከል በአሁኑ ሰዓት ዘረኝነት እና የጥላቻ ንግግሮች ሀገራትን እየፈተነ ይገኛል፤የፖርኖግራፊ ሱስ የብዙዎችን ትዳር እና ቤተሰባዊ ህይወት የሚያናጋ ተግዳሮት ሆኗል፤ይህም ችግር ከሀገር አልፎ የቤተክርስቲያንም ፈተና ሆኗል። እናም እሾህን በእሾህ ነውና እየጠፋ ያለውን ትውልድ የምንታደግበት የውጊያ አውዳችን ይህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል?
ስለዚህም እንደ ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ አገልግሎትን እንደ አንዱና ዋነኛው የወንጌል ማሰራጫ መንገድ አድርገን ብዙዎችን በማግልገል ላይ እንገኛለን በዚህም በእግዚአብሔር እርዳታ በየአመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማህበራዊ ሚዲያ እና በድህረገፆቻችን እንዲሁም በሞባይል አፖቻችን እያገለገልን እንገኛለን።እርሶም እነዚህን መተግበሪያዎች በመጠቀም ወንጌልን ለወዳጆቾ በማካፈል አብረውን ሊያገለግሉ ይችላሉ።
246 3105 500 6.4 M 3110 18+2020 በቁጥር ሲገለፅ
አሶሺየትስ(ተባባሪዎች)
በኢትዮጵያ
ዲጂታል ሚሽነሪዎች
በኢትዮጵያ
ፈቃደኛ አገልጋዮች
በኢትዮጵያ
የተደረሱ
ሰዎች
የተቀበሉ
ሰዎች
እንቅስቃሴዎች
ሰዎች የተሻሉ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ለመርዳት የተቀየሰ ሲሆን በደቀ መዝሙርነት ላይ እንዲያተኩሩ እና እራሳቸውን እንዲገመግሙ ያግዛቸዋል
ጡሩምባ ግለሰቦች እና መሪዎች ዋትስአፕን በመጠቀም ውይይቶችን እንዲገነቡ ለመርዳት የተፈጠረ ስርዓት ነው ፡፡
“ጨዋ ቃል” የሞባይል አፕሊኬሽን ሲሆን ከ 3-7 ዓመት ለሆናቸው ልጆች መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ እንዲያውቁ ይርዳቸዋል።
የፈጣን መልእክት አቅምን በመጠቀም ከስነ-ምህዳራችን ጋር ማጣመር።
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
ለምን ብቻዎትን ይጨነቃሉ? እኛም ገመና አለን ገመናዎትን ያካፍሉን።
በየቀኑ ወደ ኢየሱስ እንድትቀርብ ለማድረግ ታስቦ የተሠራ ነው
©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።