በዲጂታል ስትራቴጂ አገልጋዮች

ቶኩማ ይገዙ

ዲጂታል ስትራቴጂስት

ቶኩማ ይገዙ ሚስዮናዊ (በዲጅታል) ሲሆን የእግዚአብሄርን ጥሪ በመከተል በእግዚአብሄር መንግስት ዉስጥ እያገለገለ ይገኛል።

በ2008 በሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ የተመረቀዉ ቶኩማ፣ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ እያለም ለጠፉት ነፍሳቶች እና ስለ ወንጌል ልቡ ይቃጠል ነበር። በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ - ዲጅታል ስትራቴጂ ቡድን የሚሰጠዉን ስልጠና እሱም እንዴት ቴክኖሎጂን ተጠቅመን ወንጌልን እንስራ የሚለዉን ከወሰደ በኋላ በነበረበት ፌሎሺፕ ዉስጥ ቡድን በማቋቋም ተማሪዎች ሙያቸዉን እሱም ፎቶ ማንሳት፣ ዲዛይን እና ኮዲንግ ተጠቅመዉ ወንጌልን እንዲሰሩ ይረዳቸዉ ነበር።

አሁን ቶኩማ በዲጅታል ሚሲዮን ቡድን ስር አባል ሆኖ፣ በየዩኒቨርሲቲዉ ያለዉን የዲጅታል እንቅስቃሴን እያስተባበረ ይገኛል። በራሱም ቪድዮ ኤዲቲንግ፣ ፎቶግራፊ እና ሲኒማቶግራፊን በመጠቀም ወንጌልን እየሰራ ይገኛል።

ስለ ቶኩማ ይበልጥ ለማወቅ፦

https://www.facebook.com/tokumay

ቶኩማ ይገዙን ይደግፉ

©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።