በዲጂታል ስትራቴጂ አገልጋዮች

ዮናታን ሀይሉ

የነፃ ህይወት ቡድን መሪ

ዮናታን ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን የመጀመሪያ ድግሪውን በጤና ሳይንስ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ድግሪውን ደግሞ በዴቨሎፕመንት እና ቲዮሎጂ ከኢገስት አግኝቷል። ጌታን እንደግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለው ገና የ11ዓመት ታዳጊ እያለ ነው። የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ከነበረበት ጊዜ አንስቶም በተለያዩ ወጣቱን በተመለከቱ የቤተክርስቲያንና የተማሪዎች ህብረት አገልግሎቶች ውስጥ በማገልገል አሳልፏል።

በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ አገልግሎት ውስጥ መሳተፍ የጀመረው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት አስተባባሪ በነበረበት ጊዜ  ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታውም ሆነ በስራ ዓለም እያለ በቮለንተርነት እና በአሶሼትነት ሲያገለግል ቆይቶ በመስከረም 2010 ዓም በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪን ተቀላቅሏል።

ዮናታን ከልጅነቱ ጀምሮ በውስጡ የነበረውን ወጣቶችን በሁለንተናዊ መልኩ የማገልገል ጥሪ ላይ ትኩረት በማድረግ በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ዲጂታል ስትራቴጂ ክፍል ውስጥ የነጻ ሂወት አገልግሎት ቡድን መሪ በመሆን በተለያዩ ወቅታዊ ተግዳሮቶች እና በሱስ ቀንበር ስር የተያዙ ወጣቶችን በመድረስ ነጻ የማውጣት አገልግሎት በማገልገል ላይ ይገኛል።

ዮናታንን ይደግፉ

©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።