Close
በዲጂታል ስትራቴጂ አገልጋዮች

ሰናይ ቁምላቸው

የዲጂታል ሚሽን ቡድን መሪ

ሰናይ ስለዲጂታል ስትራቴጂ ፍላጎት ያደረበት ገና የሃይስኩል ተማሪ እያለ ሲሆን ዘወትር ከጉዋድኞቹ ጋር ቤተክርስቲያን በኢንተርኔት እና በማሀበራዊ ሚዲያ ላይ አገልግሎት ብትጀምር ምን ያህል ብዙዎችን መድረስ እንደምትችል ይወያዩ ነበር።በአጋጣሚም የዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ እያለ ከግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ የዲጂታል ሚሸን አገልጋዮች ጋር የመገናኘት እድል ገጠመው።ይህም በልቡ የነበረ ሃሳብ በመሆኑ ከዛን ጊዜ ጅምሮ በበጎ ፈቃድ የኦንላይን ሚሲዮናዊነት ማገልገል ጀመረ። በእግዚአብሄር እርዳታም በጊቢው በነበረ የተማሪዎች ህብረት ውስጥ ቀጥሎም በአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ የዲጂታል ስትራቴጂ አገልግሎት እንዲጀመር አድርጉዋል።ይህም አግልግሎት በሌሎች አቢያተክርስቲያናት እና ህብርቶች ላይ እንዲጀምር እየተዘዋወረ የዲጂታል አገልጋዮችን የማሰልጠን እና የማስታጠቅ ስራዎችን ይሰራ ነበር። ይህንም ስራ የበለጠ ለማስፋት እና ጥሪውንም ለመፈጸም ያስችለው ዘንድ ከ መስከረም 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያን ተቀላቀለ።

 

ሰናይ ቁምላቸው በአሁን ሰዓት የዲጂታል ሚሽን ቲም መሪ በመሆን የግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵይ የዲጂታል ስትራቴጂ ቢሮ ውስጥ ያገለግላል።

ሰናይ ቁምላቸውን ይደግፉ

©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።