በዲጂታል ስትራቴጂ አገልጋዮች

ትንሳኤ ፍቃዱ

ዲጂታል ስትራቴጂስት

ትንሳኤ ፍቃዱ ኮምፒውተር ኢንጂነርና ፊልም ሰሪ ነው።

በፊልም፥ በቴክኖሎጂና በሌሎች በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሳትፏል።

በፊት የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ አማኝ የነበረ ሲሆን ወደ ክርስቶስ የመጣው በታዳጊነት እድሜው ነው። በክርስትና ሕይወቱ እያደገ ሲመጣ፤ እግዚአብሔርን ይበልጥ እየወደደና በመንግስቱ ስራ ላይም ለመሳተፍ በይበልጥ ፍላጎቱ እየጨመረ መጣ።

ፊልምን ተጠቅሞ የእግዚአብሔርን እሴቶች በማጉላት ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለመጥራት ፊልም ሰሪ መሆን ይመኝ ነበር።

በመሰል ስብስቦች ውስጥም መሳተፍ ጀመረ፤ በዚህ መሃል ከግሬት ኮሚሽን ዲጂታል ሚሲዎኖች ጋር ተገናኝ። በዚህም ደግሞ ተነሳሳ።

 

አሁን ማህበረሰቡን ለመድረስ የሚጠቅሙ የፈጠራ ስራዎችን በከፍተኛ መነቃቃት እየሰራ ይገኛል።

©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።