ደቀመዛሙርትን ማፍራት

ማወቅ ያለብዎት ነገሮች

ሪች አትኪንሰን

 

ዶ/ር ታሪኩ ያደገው በኢትዮጵያ በጊ በሚባል አካባቢ ሲሆን ወላጆቹ በፍቺ የተለያዩት ገና የ1 ዓመት ህፃን እያለ ነበር::

የተለምዶ የሆነውንና እናትህ ከተወችህ ማንም ሊወድህ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ ይዞ አደገ::

ዶ/ር ታሪኩ ወንድሙ ስለ ኢየሱስ እስከነገረው ጊዜ ድረስ ህይወቱ የህመም፣ የብቸኝነትና የተስፋ መቁረጥ ነበር:: ከዚያ ቀን በፊት “ፍቅር የሚባለውን ቃል” ሰምቶ አያውቅም ነበር::

በ13 ዓመቱ ዶ/ር ታሪኩ እምነቱን በክርስቶስ ላይ በማድረግ ለሌሎች ሁሉ ስለጌታ ለመናገር ተነሳሳ:: ከዚያች ቀን ጀምሮ የሚባዛ ደቀመዝሙር ለመሆን ፍላጎት አደረበት፤ ይህንንም 25 ለሚጠጉ አመታት ሲያከናውን ቆይቷል::

አሁን ከክሩ (Cru) ጋር አብሮ እየሰራ በዙምባቡዌ ውስጥ እየኖረ ይገኛል:: በ24 የአፍሪካ ሀገራት የሚባዙ ደቀመዛሙርትን በማነሳሳት ላይ ይገኛል::

ዶ/ር ታሪኩ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ስድስት መርሆች ማንኛውም ሰው ክርስቶስን ያማከለ የሚባዛ ደቀመዝሙር እንዲሆን ይረዱታል ብሎ ያምናል:: ይህም ከልብ የመነጨ ፍላጎቱ ለሰዎች ካለው ፍቅርና ሰዎችን እስከመጨረሻው ለመርዳት ካለው ፍላጎት የመነጨ ነው::

1. በፆምና በፀሎት ጀምር

ዶ/ር ታሪኩ ቦስኮ የሚባል በሩዋንዳ የሚኖር የመጀመሪያ ዓመት የኮሌጅ ተማሪን ያስታውሳል:: ቦስኮ “ሩዋንዳን በወንጌል የመገለባበጥ” ፅኑ ፍላጎት ነበረው:: የተማሪዎች መሪ ሳለ በ4 ዓመታት ብቻ የክርስቲያን ተማሪዎች ማዕከል ከ1 ወደ 38 (ከ1 ዩኒቨርሲቲ ወደ 14 ዩኒቨርሲቲ) እንዲያድጉ ረድቷል:: ይህ ሊሆን ከቻለባቸው ምክንያቶች አንዱ ለ40 ቀናት በጥቅምትና በህዳር ወራት በሩዋንዳ የፆምና ፀሎት ጊዜ በመኖሩ ነው:: የተለያዩ ሀገራትንና ካምፓሶችን በወንጌል ለመድረስ ዶ/ር ታሪኩ ከ7 እስከ 40 ቀናት ድረስ ፆምና ፀሎት እንዲደረግ ይመክራል:: 

ፀሎት አክብሮት መስጠት፣ ምስጋና፣ ንስሀ፣ ምልጃና ልመናን ያጠቃልላል:: ዶ/ር ታሪኩ “ፀሎት የህይወት ዘይቤ ነው” ይላል:: ስትቀመጥም ሆነ ስትነሳ እንደሚያስፈልግህ እንደ እስትንፋስህ ነው::

2. በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ላይ ተመርኮዝ

“መንፈስ ቅዱስ በአንተ ውስጥ ሲኖር ወደ ራስህ አትመለከትም” ይላል ዶ/ር ታሪኩ:: ባለፈው ዓመት በዛምቢያ ብቻ ራሔል የተባለችው የዛምቤያው ክሩ ቅርንጫፍ አገልግሎት ባልደረባ (ዶ/ር ታሪኩ የሚከታተላት) ያሰለጠነቻቸው ተማሪዎች አራተኛ መንፈሳዊ የደቀመዝሙር ትውልድ ላይ ደርሰዋል:: በአሁኑ ወቅት ደግሞ 75 የሚሆኑ ደቀመዛሙርት ወደ 225 ለማደግ በመሰልጠን ላይ ይገኛሉ::

“አገልግሎቴ በተማሪዎች የሚመራ ነው” የሚለው ዶ/ር ታሪኩ “የሹፌሩ መቀመጫ ላይ ከዚህ በኋላ የለሁም” ይላል፡፡

3. ሌሎች በእምነት ሆነው እንዲወጡ እርዳቸው

ዶ/ር ታሪኩ በኢትዮጵያ ከሚኖር ምስጋናው ከተባለ ተማሪ ጋር ተገናኝቶ ቡና እየጠጡ ተጨዋወቱ፡፡ ምስጋናው ከገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል ወደ ከተማ በመምጣቱ ዓይናፋርና የሚፈራ ሰው ነበር:: የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቁንቋን መናገር ባይችልም መሠረታዊ የንግድ ቋንቋን ይችል ነበር:: ምስጋናው ክርስቲያን ሲሆን ዶ/ር ታሪኩም ለወንጌል ያለውንም ጥልቅ ፍቅር ተመለከተ፡፡ ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ጥናት ጋብዞት በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጲያ በተዘጋጁ መከታተያ የትምህርት መረጃዎች ደቀመዝሙርነትን አስተማረው፡፡ 

ለምስጋናው እየፀለየና እያበረታታው በክርስቶስ ያለውን ማንነቱን እንዲያውቅም ረዳው፡- “ልታደርገው ትችላለህ:: አንተ የክርስርስቶስ አምባሳደር ነህ” እያለ ይነግረው ነበር፡፡

ከአራት ወራት በኋላ ምስጋናው በመውጣት እምነቱን ማካፈል ጀመረ:: ሦስት ተማሪዎችም ክርስቶስን ተቀበሉ:: እያስተማረና ደቀመዝሙርነትን እያሰለጠናቸው በ6 ወር ውስጥ ቡድኑ ወደ 10፣ ከአንድ አመት በኋላም ወደ 120 ሰዎች አደገ፡፡

4. ደቀመዛሙርት ሃላፊነት እንዲቀበሉ አድርጋቸው

ጆን የተባለው ተማሪ መሪነትን እንዲቀበል ሲጠየቅ እንደሚችል እርግጠኛ አልነበረም:: ብቁ እንደሆነ ሊያምን አልቻለም ነበር :: አንድ ቀን ለብዙ ሰዓት ያህል ወንጌልን ለሌሎች ለመናገር ወጣ:: ካናገራቸው ሰዎች መሃል አራቱ እምነታቸውን በክርስቶስ ላይ ለማድረግ ፍላጎት አሳዩ:: ነገር ግን ከእነርሱ ጋር ከመፀለይ ይልቅ ዶ/ር ታሪኩ መጥቶ እንዲፀልይላቸው ጠየቀው:: ዶ/ር ታሪኩም ጆንን ላለማሳፈር ጥያቄውን ተቀብሎ ፀለየላቸው:: ከዚያ በኃላ ግን ዶ/ር ታሪኩ ጆንን ለብቻው በማናገር ለፀሎት እርሱ መጥራት እንደማያስፈልገው ነገረው:: በሚቀጥለው ጊዜ ጆን 17 ሰዎችን ወደ ጌታ ሲመራ ለእያንዳንዳቸው ራሱ እየፀለየ ነበር::

5. ደቀ መዛሙርት እንዲሳሳቱ ፍቀድላቸው

ዶ/ር ታሪኩ ደቀመዛሙርት በመጀመሪያ ጊዜ ነገሮችን በትክክል ላይሰሩ እንደሚችሉ ያውቃል:: “አንተ ማስተማር እንደምትችለው ማስተማር ባይችሉም ከአንተ ግን መማር ይችላሉ:: በመሳሳት ሊወድቁ እንደሚችሉ እያሰብክ መሳሳት እንዲችሉ ነፃነትን ስጣቸው” ይላል::

6. ስለ መልዕክትህ አስብ

አንተ የወንጌልን መልዕክት ለደቀመዛሙርት የምታስተምር መልዕክተኛ ነህ:: ባህሪህ የመልዕክትህን ያህል አንዳንዴም ደግሞ በበለጠ ለሰዎች ምስክር ሊሆን ይችላል ይላል ዶ/ር ታሪኩ:: ታማኝ ነህ? በጌታ ያለህ የግል ህይወትህ እንዴት ነው?

በተጨማሪም መልዕክትህን አስብ:: ቀላልና ግልጽ ነው? በልዩ ልዩ ባህሎች ውስጥ መሰማት የሚችል ነው?

መልዕክትህን እንዴት ትናገራለህ? ዘዴዎችህስ ምንድናቸው? ዶ/ር ታሪኩ ዘዴው እንደ እግር ኳስ ቀላል ነው ይላል:: በሁሉም ቦታ ታዋቂና እንደሆነው እንደ ስፖርቱ መሰረታዊ መርሆ የማይከብድና ዝም ብሎ ኳሱን የመምታት ያህል ነው:: የወንጌል መልዕክትህን ወደዚያ ዓይነት ዕይታ ማምጣት ትችላለህ?

ለዶ/ር ታሪኩ የሚባዙ ደቀመዛሙርትን መፍጠር ማለት ተስፋ ለሌላቸው ተስፋ መስጠት ነው::

“ተስፋ ያጡ ሰዎች ጌታን ሲያገኙ ተስፋን ያገኛሉ:: ለእኔ ወንጌልን መስበክና ደቀመዛሙርን ማፍራት እጅ ለእጅ የሚሄዱ ነገሮች ናቸው:: ዓለምን በራስህ ብቻ መድረስ አትችልም” ይላል፡፡

©ግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ። መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።